የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ “ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ” በሚለው ሀሳብ መሉ እምነት አላት – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

By Tibebu Kebede

March 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ “ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ” በሚለው ሀሳብ መሉ እምነት እንዳላት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አረጋገጡ።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንትና ከወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ፌሊክስ ሺሴኬዲ ከተላከ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በፕሮፌሰር አልፎንስ ንቱምቤ ሉአባ የተመራው ቡድን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ በሚደረገው ድርድር ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር ላይ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅም ኢትዮጵያ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚጠቅም መፍትሄ ላይ ለመድረስ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በዚህም ዕለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ” በሚለው መርህ ለማስኬድ ኢትዮጵያ ምን ጊዜም ዝግጁ መሆኗን አስምረውበታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!