Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአዲሷ የአሜሪካ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአዲሷ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው የሃገራቱን የረጅም ጊዜ ወዳጅነት በማድነቅ፤ በተለይም በትምህርት፣ በጤና እና በደህንነት ጉዳዮች ላይ ያለው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተስማምተዋል፡፡
ሃገራቱ በትምህርት፣ በጤና፣ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ሃገራቱ ያላቸውን ትብብብር ማሳደግ እንዳላበቻውም አንስተዋል፡፡

አቶ ደመቀ በበኩላቸው መንግሰት በትግራይ ክልል አስገዳጅ ሁኔታ ስለነበረ እና ሰላማዊ አማራጮች በህወሓት ቡድን ተቀባይነት በማጣታቸው ተገዶ ወደ ሕግ ማስከበር እርምጃ መግባቱን አስረድተዋል፡፡

ከዘመቻው በኋላ ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ እና ክልሉን መልሶ ለማቋቋም በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

በክልሉ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶች እና መገናኛ ብዙሃን ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን አቶ ደመቀ ለአምባሳደሯ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ እስካሁን ለ3 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች መሰራጨታቸውን አውስተዋል፡፡

ከዚህ ድጋፍ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነው በመንግስት መሸፈኑን ጠቁመው፤ ዓለም አቀፉ ማህበረስብ ተጨማሪ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.