Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል 5 ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ስራ ጀምረዋል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰብሳቢነት የሚመራው የብሄራዊ ድንገተኛ አደጋ አስተባባሪ ማዕከል የሚኒስትሮች ኮሚቴ ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

በስበሰባው የኮሚቴው አባል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በትግራይ ክልል እና በመተከል ዞን በማድረግ ላይ ስላሉት የአስቸኳይ እርዳታ አቅርቦትና ስርጭት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ እያቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከጊዜያዊ የእርዳታ አቅርቦት ባሻገር ህዝቡን በቋሚነት መልሶ የማቋቋምና ወደ መደበኛ ህይወት የመመለስ ስራ በተጓዳኝ እየተካሄደ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተወካዮች የዕርዳታ ስርጭቱና ክፍፍሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ እያለ መምጣቱን አረጋግጠዋል፡፡

በክልሉ ያለው አጠቃላይ ሁኔታም እየተሻሻለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት አምስት ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ስራ መጀመራቸውን እና ከእነዚህ አምስት ፋብሪካዎች ውስጥ አንዱ ለውጭ ገበያ አቅርቦት መጀመሩን መናገራቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.