Fana: At a Speed of Life!

አይ ሲ ሲ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለጥቃት ሰለባዎች 30 ሚሊየን ዶላር ፈረደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት /አይ ሲ ሲ/ ዳኞች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአማጽያን በተፈጸመ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሰዎች 30 ሚሊየን ዶላር እንዲሰጣቸው ፈረደ፡፡

የፍርድ ቤቱ 30 ሚሊየን ዶላር ውሳኔ በአማጺ መሪው ቦስኮ ንታጋንዳን ሰለባ የሆኑ ህጻናት ወታደሮችን፣ የአስገድዶ መድፈርና የወሲብ ጥቃት ለደረሰባቸው የሃገሬው ዜጎች የሚውል ነው፡፡

የአማጺ መሪው በፈረንጆቹ 2019 በሰው ልጆች ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች እና በጦር ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብሎ የ30 ዓመት እስር ተፈርዶበታል፡፡

በሃገሪቱ በማዕድን በበለጸገው አካባቢ ከፈረንጆቹ 2002 እስከ 2003 ድረስ በተነሳ የብሄር ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ለህልፈት ሲዳረጉ በሺህዎች ደግሞ ተሰደዋል፡፡

አይ ሲ ሲ በአሁኑ ወቅት ትረስት ፈንዱ ላይ በቂ ገንዘብ እንደሌለው ጠቅሶ ነገር ግን የገቢ ማሰባሰቢያዎችን እንደሚያካሂድ አስውቋል፡፡

በተጨማሪም የአማጺ መሪው እስካሁን ይፋ ያልወጣ ንብረት ካለው በሚል በድጋሚ የማጣራት ስራዎችን እንደሚሰራም ነው ዳኞቹ የገለጹት፡፡

 

ምንጭ፡-አልጀዚራ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.