Fana: At a Speed of Life!

ባህሬን በትግራይ ክልል ያለው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ገለጸች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባህሬን በትግራይ ክልል ያለው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ገለጸች።
በባህሬን የኢፌዴሪ ቆንስላ ጀኔራል ጽህፈት ቤት ቆንስል ጄነራል አምባሳደር ጀማል በክር ከባህሬን ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ሻይካ ራና ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር አለመግባባት፣ በዜጎች መብትና የበረራ አገልግሎት በሁለቱ እህትማማች አገሮች መካከል ስለሚጀመርበት ሁኔታ መክረዋል።
በዚሁ ወቅት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በትግራይ ክልል ያለው የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን አመልክተዋል።
አያይዘውም ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር አንጻር ሶስቱ አገራት በትብብርና በውይይት እንዲፈቱ አገራቸው እንደምታምንና እንደምትደግፍ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.