Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር በሁለትዮሽ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር በነበራቸው ውይይት በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ፣አሁን እየተከናወነ ያለው የመልሶ ግንባታ ስራ እና የሰብዓዊ ድጋፉ በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን ገልጸዋል።
አቶ ደመቀ አያይዘውም ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ጉዳይ ኢትዮጵያ በድርድር ለመፍታት ጽኑ አቋም እንዳላትም ነው የተናገሩት።
ከዚያም ባለፈ ባለስልጣናቱ በውይይታቸው የሀገራቱን ግንኙነት መሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
እንዲሁም ለቀጠናዊ መረጋጋት እና አቅም ግንባታ ትብብርን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን መሪዎቹ በምክክሩ ላይ አንስተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.