Fana: At a Speed of Life!

የኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል 105 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል 105 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት፡፡
ለኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ ማስጀመሪያ የሚሆን 105 ሚሊየን ብር የሚገመት ሁለት ኮንቴይነር የህክምና ቁሳቁሶች መግባታቸው የተገለፀ ሲሆን የፅኑ ህሙማን መታከሚያ (ICU) ፤ አልጋዎች ፡ አልትራሳውንድ, እና ሌሎች እቃዎች የተካተቱበት ነው ተብሏል፡፡
የህክምና እቃዎቹ ቀለም አትዮጵያ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅንጅት እንዲሁም ከዩናይትድ ሪሊፍ ሰርቪስ( United relief Service) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተገኙ እንደሆነ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ኢንጅነር ከማል መሀመድ ገልጸዋል።
ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ለሁሉም ባለድርሻ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አያይዘውም የጉምሩክ ሂደቱን እንደጨረሰ እቃዎቹ ወደስራ እንደሚገቡ ገልጸው÷ይህ ጥረትም የሆስፒታሉን ችግር በከፊልም ቢሆን የሚቀርፍ ይሆናል ብለዋል፡፡
ጂቡቲ ወደብ የደረሱና እየመጡ ያሉ ተጨማሪ ኮንቴይነሮች ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል፡፡
በይክበር አለሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.