የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ 137 ነጥብ 35 ሚሊየን ዶላር የእርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ

By Tibebu Kebede

March 10, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ 137 ነጥብ 35 ሚሊየን ዶላር የእርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሪት ያስሂን ወሀብራቢና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬከተር ኦስማን ዲዮን ተፈራርመውታል።

ስምምነቱ ዓለም አቀፍ አጋርነት ለትምህርት በተሰኘው ማእቀፍ አማካኝነት የተደረገ ነው፡፡

ከዚህ ውስጥ 14 ነጥብ 85 ሚሊየን ዶላሩ በዓለም አቀፍ አጋርነት ኮቪድ19 በትምህርቱ ዘርፍ ላስከተለው ተፅዕኖ ምላሽ ለመስጠት የሚውል ነው ተብሏል፡፡

በዚህም በቫይረሱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት እንደገና ማስቀጠልና በቀጣይም ከቫይረሱ ለማገገም የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ቫይረሱን ለማቆጣጠር የሚሰሩ ተግባራትን ለማገዝ የሚውል ነው፡፡

ከዚህ ባለፈም ቀሪው 122 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላሩ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝና ለመደገፍ የሚውል መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!