የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ከፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሃላፊ ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

March 10, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ከፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሃላፊ ሜጀር ጄኔራል ሎረን ማርበፍ ጋር ተወያዩ፡፡

በወቅቱም በሁለቱ ሃገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አምባሳደር ሄኖክ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሁለቱ ሃገራት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይም ሃሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

በተጨማሪም ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር ማጠናከር በምትችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መክረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!