Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ሕዝብ ሀገር ያጸና፣ ለሀገር መስዋዕትነት የከፈለ ነው፤ ይህን የሚገፋ አካል ካለ ‘ታሪክ ያበላሻል’ -ዶ/ር አብርሃም

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የራሳቸውን ፍላጎት ለሟሟላት ለሚሯሯጡ ቡድኖች ተብሎ የሚፈርስ ሀገር የለም ሲሉ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለፁ።

ሚኒስትሩ የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያን ከገነቡ ሕዝቦች አንዱ መሆኑንም ነው የገለጹት።

ይሁንና የሕዝብ ሳይሆን የቡድንና የግል አጀንዳ በማስቀደም ሀገር ለማበላሸት የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን ጠቁመዋል።

የእነዚህ ሕልመኞች ፍላጎት እንዳይሳካ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ በመሆን የሀገሩን አንድነት ለማስቀጠል መስራት አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

‘ኢትዮጵያዊያን አንድነታችን የሚጠናከረው ስንደጋገፍ ስንረዳዳና የአንዱ ችግር የሌላችን መሆኑን ስናረጋግጥ ነው’ ብለዋል።

ሀገር የሚገነባው በአብሮነት፤ ሲቸገር በመተጋገዝ ሲደሰት አብሮ በመደሰት ነው ያሉት ዶክተር አብርሃም ኢትዮጵያ አንድ አካል ነች አንገቷን መቁረጥ አይቻልም ሲሉ ገልጸዋል።

የትግራይ ሕዝብ ሀገር የመሰረተ፣ ሀገር ያጸና፣ ለሀገር መስዋዕትነት የከፈለ ነው፤ ይህን የሚገፋ አካል ካለ ‘ታሪክ ያበላሻል’ ብለዋል።

ዶክተር አብርሃም የትግራይ ሕዝብ ሲቸገር ብቻችሁን የምትወጡት ችግር የለም በማለት ድጋፍ እያደረጉ ለሚገኙ ክልሎች ሕዝቦችና አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.