ቢዝነስ

የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ በመጭው ቅዳሜ ይመረቃል

By Tibebu Kebede

March 10, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ በመጭው ቅዳሜ ይመረቃል፡፡

በ294 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ፓርኩ 152 ሺህ ሼዶች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፓርኩ የአቮካዶ ዘይት፣ የአቮካዶ ማር፣ ቡደና ካፕ እና ጆጆ የተሰኘው በተለያዩ ጣዕሞች የተዘጋጀ ወተት አምራች ፋብሪም ስራ ጀምረዋል፡፡

የወተት ፋብሪካው በቀን 60 ሺህ ሊትር የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፥ አሁን ላይ በቀን 30 ሺህ ሊትር ወተት እያመረተ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የአቮካዶ ምርት በማቅረብና ለወተት ፋብሪካው ግብአት በማቅረብ በአካባቢው የሚገኙ አርብቶና አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል ተብሏል፡፡

የደቡብ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩ ወልዴ በፓርኩ የሚመረተውን የአቮካዶ ዘይት 17 ጊዜ ወደ ውጭ መላክ መቻሉን ገልፀዋል።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኩ 13 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ የኮንክሪት አስፓልት መንገድን ጨምሮ ለአምራቾች አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶችም ተሟልተዋል ነው የተባለው፡፡

በመቅደስ አስፋው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!