Fana: At a Speed of Life!

ሱዳን በዳርፉር የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ኃይል የሚወጣበት ጊዜ እንዲዘገይ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን በዳርፉር የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ኃይል /ዩናሚድ/ የሚወጣበት ጊዜ እንዲዘገይ ጠየቀች፡፡

ካርቱም ካልማ እና ሶርቶኒይ በተባሉ የጸጥታ ስጋት ባለባቸው ሁለት ካምፖች ሰላም አስከባሪው እንዲቆይ ፍላጎት አላት ተብሏል፡፡

በሁለቱ ካምፖች ሃይል እስከሚሰፍር ድረስ ነው ጥያቄዋን ለተመድ ያቀረበችው፡፡

የተባበሩት መንግስታት የመስክ ድጋፍ መምሪያ ኃላፊ አቱል ኻሬ ለጥያቄው አወንታዊ ምላሽ ለመስጠት ማሰባቸውን ገልጸዋል፡፡

በካልማና ሶርቶኒይ የሚገኙ ነዋሪዎች የሰላም አስከባሪውን ኃይል መውጣት ተቃውመው በተደጋጋሚ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

ተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይሉና ሲቪሎች እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ እንዲወጡ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡- ሱዳንትሪቢዩን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.