Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር ስድስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዛሬው መርሃግብር የምክርቤቱ 16ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔ አስተያየት ተሰጥቶበት ይጸድቃልም ተብሎ ይጠበቃል።

የተጠቃለለ የአስፈጻሚ አካላት የ2013 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይትም ይደረግበታል።

ነገ መጋቢት 03/2013 ዓ.ም ቀጥሎ በሚካሄደው ጉባዔ ደግሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2013 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ብዙኀን መገናኛ ድርጅት የ2012 በጀት ዓመትና የ2013 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በውይይት እንደሚጸድቅም በመርሃግብሩ ተመላክቷል።

መጋቢት 04/2013 ዓ.ም የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ፣ ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ ረቂቅ አዋጅ ቀርቦ በውይይት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚሁ ዕለት የአብክመ ሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ማሻሻያ ቀርቦ ይጸድቃል ነው የተባለው።

አብክመ የቴምብር ቀረጥ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣ የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል፣ የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅም በውይይት ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አብመድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.