ቢዝነስ

የጋናው ኤምፋርማ በኢትዮጵያ በመድሃኒት አቅርቦት ሊሰማራ ነው

By Tibebu Kebede

March 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤምፋርማ የተሰኘው የጋናው መድሃኒት አቅራቢ ኩባንያ በኢትዮጵያ በመድሃኒት አቅርቦት መሰማራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን ከበላይአብ ፋርማሲዩቲካልስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር መፈራረሙን አስታውቋል፡፡

የኤምፋርማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ግሪጎሪ ሬክሰን ስምምነቱ በኢትዮጵያ የህክምናውን ዘርፍ ለማገዝና መድሃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!