Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ስርአት ማዘመኛ የ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያዎች ስርአት ማዘመኛ የ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የክፍያ ስርአቱን መሠረተ ልማት ለማዘመን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሚመራው ለኢት ስዊች አክሲዮን ማኅበር ድጋፉን አፅድቋል፡፡
የአሁኑ ድጋፍ በአፍሪካ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ስርአትን ለማስፋፋት ከተቋቋመው አፍሪካ ዲጂታል ፋይናንሺያል ፋሲሊቲ ከተባለው የባንኩ ልዩ የፈንድ ስርዓት የተገኘ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ድጋፉ በአፍሪካ በባንክ የማይጠቀሙ 332 ሚሊየን ሰዎች የዲጂታል የክፍያ ስርአት ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.