Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስቴር ከሁለት ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የግብርና ሚኒስቴር  ከናሽናል አቪዬሽንና ከሙሃመድ ሃሚድ የቁም እንስሳት ንግድ ከተሰኘ የሳውዲ አረቢያ ኩባንያ ጋር ነው የተፈራረመው።

ሚኒስቴሩ አንበጣን ለመከላከል የሚውሉ የአውሮፕላን ግዢዎችን ለማድረግና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት ነው ከናሽናል አቪየሽን ኩባንያ ጋር የተፈራረመው።

ኢትዮጵያ ባለፉት 20  ወራት ብቻ አንበጣን ለመከላከል ከ4 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማውጣቷ ተነግሯል።

ከዚህ ውስጥም ከፍተኛው ለአውሮፕላን ኪራይ መሆኑ ተነስቷል።

ይህ ስምምነት ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አልፎ ሃገሪቱ ለዚህ የምታወጣውን ወጪ በከፍተኛ መጠን ይቀንሳልም ነው የተባለው ።

ከዚህ ባለፈም የተዛማችና ወረርሽኝ ተባዮችን በራስ አቅም መከላከል የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

የግብርና ሚኒስቴር በተመሳሳይ ከሳውዲ አረቢያ የቁም እንስሳት ንግድ ኩባንያ ከሆነው የሙሃመድ ሃሚድ የቁም እንስሳት ንግድ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።

ሚኒስቴሩ ሃገሪቱ  ለውጭ የእንስሳት ንግድ ከገነባቻቸው ማቆያዎች ውስጥ አንዱን ማቆያ ኩባንያው  አገልግሎት እንዲሰጥ ተፈራርሟል።

በሃገሪቱ ያለው እንስሳት ማቆያ ክፍተት ያለበት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ ይህ  ስምምነት ያለውን ውስንነት በእጅጉ ይቀርፈዋል ተብሎ ታምኖበታል።

ሚኒስቴሩ በዘርፉ ባለሃብቱን በማሳተፍ አሠራሩን ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ እየሰራ ነው ተብሏል።

የዛሬው ስምምነትም የዚሁ አካል መሆኑ ተገልጿል።

በሀይማኖት እያሱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.