Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ከተማ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ከተማ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ኪነጥበብ ሀገርን በመገንባት ፣ ዜጋን ለመቅረጽ፣ ሰላም እና አንድነትን በማጠናከር እና ህዝብን ለልማት በማነሳሳት ትልቅ መሣሪያ ነው ብለዋል ።

የከተማዋን ህብረተሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲሳኩ፣ የታየው የሰላም እና ሀገራዊ አንድነት ይበልጥ እንዲጠናከር የኪነጥበብ ባለሙያዎች በሙያቸው እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሀገራዊ ለውጡ እንዲመጣ የተጫወቱት ሚና የላቀ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ለውጡ ቀጣይነት እንዲኖረው በሙያቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኪነጥበብ ዘርፉን ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን የገለፁት ወይዘሮ አዳነች የአድዋ ዜሮ ኪሎሜትር ሙዚየም እና ሌሎች ፕሮጀክቶች የባህል እና የኪነጥበብ ማንጸባረቂያ ናቸው ብለዋል ።

ከውይይቱ በኋላም የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ከኢትዮጵያ የኪነጥበብ ማህበራት ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.