Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የቴሌኮሙኔኬሽን ልማት ጉባኤ ዝግጅት አህጉራዊ ስብሰባዎችን እንድትመራ ተመረጠች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በቀጣይ አመት በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የአለም አቀፍ የቴሌኮሙኔኬሽን ልማት ጉባኤ ዝግጅት አህጉራዊ ስብሰባዎችን እንድትመራ ተመረጠች።

የ2021ንዱን አለም አቀፍ የቴሌኮም ልማት ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በቀጣይ አመት አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል።

ለጉባኤው ስኬት ኢትዮጵያ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገች ሲሆን÷ የጉባኤውን አህጉራዊ ስብሰባዎች በሊቀመንበርነት እንድትመራም ተመርጣለች።

ስብሰባውን በሊቀመንነት እንዲመሩ የተመረጡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር አህመዲን መሀመድ ÷ለጉባኤው መሳካት ውጤታማ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንደሚያከናወኑ ቃል ገብተዋል።

በአህጉራት መከካል የሃሳብ ልውውጥ በማድረግ፣ ፍሬያማና ቀልጣፋ የዝግጅት ስራዎች እንዲከናወኑ ኢትዮጵያ ትሰራለች ያሉት ሊቀመንበሩ÷ በኮቪድ ተፅዕኖ ውስጥ ስኬታማ ስራ እንደምታከናውን ቃል ገብተዋል።

የጉባኤው አስተናጋጅ ሀገር አህጉራዊ ስብሰባዎችን እንድትመራ መደረጓ ለኮንፈረንሱ የሚደረጉ ዝግጅቶች በፍጥነት እንዲከናወኑ እድል ይሰጣልም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ከተሳታፊ ሀገራት የቀረቡ ኮቪድ የደቀናቸው ስጋቶችን የተመለከቱ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አቅርባለች።

ከተለያዩ የአለም ሀገራት የተውጣጡ 325 ሰዎች የተሳተፉበት ስብሰባ በበይነ መረብ መካሄዱን ከኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.