የሀገር ውስጥ ዜና

ብልጽግና ፓርቲ ዶክተር ዐቢይ አሕመድን በአጋሮ ከተማ ዕጩ ተወዳዳሪ አድርጎ አቀረበ

By Tibebu Kebede

March 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ለምርጫ በጅማ ዞን አጋሮ ከተማ ዕጩ ተወዳዳሪ አድርጎ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

ፓርቲው ዛሬ ማኒፌስቶውንና የምርጫ ምልክቱን በአጋሮ ከተማ ለአባላትና ደጋፊዎች ባስተዋወቀበት ወቅት ነው ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ዕጩ አድርጎ ማቅረቡን ይፋ ያደረገው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የአጋሮ ከተማ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ነዚፍ መሀመድአሚን በትውውቅ መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር “ፓርቲው አስከፊውን ሥርዓት ያስወገደና ለሀገራችን ትልቅ የለውጥ ብርሃን መፈንጠቅ የቻለ ነው” ብለዋል፡፡

የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለምርጫው በአጋሮ ከተማ ዕጩ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ መቅረባቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ፓርቲው ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን እንደሚወጣም የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ ገልጸዋል።

የፓርቲው የአጋሮ ከተማ ከፍተኛ አመራር አቶ ነሲብ ያሲን በበኩላቸው ብልጽግና ፓርቲ ሀገሪቱን ወደፊት ለማራመድ ያለመ ግልጽና ተጨባጭ የለውጥ መንገድ የጀመረ ፓርቲ መሆኑንና ለተሻለ ብልጽግና እንደሚሠራ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!