የሀገር ውስጥ ዜና

በኒውዮርክ እና በብራሰልስ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎችን አካሄዱ

By Abrham Fekede

March 11, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ትክክለኛ እና ወቅታዊ ገፅታ ለመላው ዓለም የሚያስተጋቡ ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፎች በካናዳ የተለያዩ ከተሞች፥ በኒውዮርክ እና በብራስልስ ተካሄደዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ጉዳይን አስመልክቶ ዕውነት እና ፍትህን በማንገብ እንዲሁም የሃሰት ውንጀላዎችን በመጠየፍ በዓለም አደባባይ በፅናት ለተሰለፋችሁ ወገኖቻችን በእጅጉ እናከብራችኋለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በምዕራቡ ዓለም በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን በማስተባበር እና በመምራት ሃገራዊ ሃላፊነታችሁን በክብር ለተወጣችሁ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

አቶ ደመቀ ቀጣይነት ላለው አንድነት እና ህብረት በጋራ እንደምንረባረብ ላረጋግጥ እወዳለሁ ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።