የሀገር ውስጥ ዜና

የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የለውጥ ስራዎች መደገፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ

By Tibebu Kebede

March 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የለውጥ ስራዎች መደገፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

በቤልጂየም ብራሰልስ በሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ፅህፈት ቤት ፊት ለፊት የኢትዮጵያን ወቅታዊ ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በትናንትናው እለት ተደርጓል፡፡

በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ዓለም አቀፍ ትብብር የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዳይሬክቶሬትም የድጋፍ ሰልፉን በተመለከተ ደብዳቤ ጽፏል፡፡

በደብዳቤውያውም ህብረቱ የተደረገውን የድጋፍ ሰልፍ እንደተመለከተው ጠቅሶ፥ ህብረቱ ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ እንደቁልፍ አጋር እንደሚቆጥራት አስታውቋል፡፡

በሃገሪቱ የሚካሄዱ የለውጥ ስራዎችን መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀው ህብረቱ፥ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ስትራቴጂክ ግንኙነት ካላቸው ጥቂት ሃገሮች መካከል አንዷ መሆኗንም ጠቅሷል፡፡

ህብረቱ የኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ጠንቅቆ ይረዳል እንደሚረዳ በማውሳትም የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል።

አያይዞም ህብረቱ በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ ቀውስ እንደሚያሳስበው በመግለጽም፥ በክልሉ ዓለም ዓቀፍ የስደተኞች እና የሰብአዊ መብት ሕግጋቶች እንዲከበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!