Fana: At a Speed of Life!

ለሞዴል አርሶ አደሮች በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለቤት መስሪያ የሚሆን የመሬት ርክክብ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከ5 ሺህ 700 በላይ ለሆኑ ሞዴል አርሶ አደሮች በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን በተለያዩ ከተሞች ላይ ለቤት መስሪያ ቦታ የሚሆን የመሬት ርክክብ አካሄደ።
መርሀግብሩ በኦሮሚያ ልዩ ዞን በሰንዳፋ ከተማ ነው የተካሄደው

በመርሀ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ሞዴል አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷ ከዚህ ቀደም በነበሩት ስርዓቶች አርሶአደሩ በተለያዩ ምክንያቶች አላግባብ መሬቱን ሲነጠቅና ለከፋ ችግር ሲጋለጥ መቆየቱን አንስተዋል።

አሁን ላይ ግን አርሶ አደሮቹ ህጋዊ በሆነ መልኩ ተደራጅተው የቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው መደረጉን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያነሱት።

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.