የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

March 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይታቸው የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት ቀጣይ አካል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በዚህ ወቅትም በተለይም በኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ አጠቃላይ ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታና ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ዙሪያ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ሁኔታ ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ እና በሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!