Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ 14 ወረዳዎች “በስማርት” ወረዳነት ተደራጁ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ 14 ወረዳዎች ለሰራተኞች እና ባለጉዳዮች ምቹ እና የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጡ “በስማርት” ወረዳነት ተደራጁ፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት አገልግሎት ፈላጊዎች ወረፋ የሚጠብቁበት፣ አገልግሎት የሚያገኙበትና የሚስተናገዱበት በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ሥርዓት ለመዘርጋት ከተማ አስተዳደሩ 121 ወረዳዎችን ወደ ስማርት ወረዳነት ለመቀየር ፕሮጀክት ነድፏል፡፡
አገልግሎት አሰጣጥን ዘመናዊ ማድረግ ብቻም ሳይሆን የተለወጠ አስተሳሰብ፣ ሕዝብን እኩል ማስተናገድ የሚችል አዕምሮና ቅንነት መላበስ ይገባዋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ ሉሌ በበኩላቸው የስማርት ወረዳዎች አተገባበር ከከተማዋ እድገትና ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም አገልግሎት ለመስጠት በመሆኑ የሚያግዙ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ቢሮውም በዚህ ዓመት ብቻ ከ93 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ አምስት የስማርት ወረዳዎችን በማደራጀት አገልግሎት ማስጀመሩንም ማስታወቃቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.