Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያ ተያዥ ግለሰብ ከተገኘ ነገ አንድ ዓመት ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ በመጀመሪያ የተያዘ ግለሰብ ከተገኘ ነገ አንድ ዓመት ይሆናል።
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘ አንድ ዓመት በሚሞላበት ዕለት የኮሮና ቫይረስ ክትባትን መስጠት ትጀምራለች።
በቻይናዋ ሁቤ ግዛት ውሃን ከተማ የተነሳው የኮሮና ቫይረስ ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ አዳርሷል።
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ከተገኘ ነገ መጋቢት 4 ቀን 2013 አንድ አመት ይሞላዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ቫይረሱ የተገኘበት ሆኖ የተመዘገበው ግለሰብ የ48 አመት የጃፓን ዜጋ ሲሆን፣ የካቲት 25 ቀን 2012 ዓ/ም ከ ቡርኪና ፋሶ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱየሚታወስ ነው።
በወቅቱ ኢትዮጵያ በሽታው ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በተዘረጋው የተጠናከረ የበሽታዎች ቅኝት ስራ፣ የመጀመሪያውን ታማሚ ለመለየት ችላ ነበር፡፡
እንዲሁም ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችም የመለየትናክትትል የማድረግ ስራ በወቅቱ ሲሰራ ነበር።
በወቅቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመለየት ስራ የተሻለ የነበረ ቢሆንም ቫይረሱ በኢትዮጵያከተገኘ አንድ ዓመት በኋላ ወደ ማህበረሱ መሸጋገሩን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ቫይረሱ እስከ አሁን በኢትዮጵያ 2 ሺህ 483 ሰዎች ለህልፈት የዳረገ ሲሆን 171 ሺህ 210 ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
ከእነዚህም ውስጥ 140 ሺህ የሚሆኑት ከቫይረሱ ማገገማቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ የሚያመለክት ሲሆን ከ27 ሺህ በላይ የሚሆኑት ቫይረሱ በአሁን ወቅት ያለባቸው ናቸው።
ኢትዮጵያ 2 ሚሊየን 207 ሺህ 195 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ አድርጋለች።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.