Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ-19 ክትባት በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ የሞጆ ፕራይመሪ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ክትባት ዛሬ መስጠት ጀምሯል።

በክትባት ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባኤ ሎሚ በዶ ፣የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግስቱ በቀለ የሞጆ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ መሰረት አሰፋን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎች ተገኝተው ክትባቱን ወስደዋል ።

በመጀመሪያው ዙር በመንግስትም ሆነ በግል የጤና ተቋማት ውስጥ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችና ይበልጥ ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንደሚደረግ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መንግስቱ ገልፀዋል።

ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ተጓዳኝ የጤና ህመም ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ወደ ሀገሪቱ ከገባ ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የስርጭት ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በሽታውን ለመከላከል የሚደረገው ጥንቃቄ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል።

እስካሁን በክልሉ 277ሺህ 421 ሰዎች ተመርምረው 25ሺህ 695 ሰዎች ቨይረሱ ተገኝቶባቸው 21ሺህ 208 ሰዎች ሲያገግሙ የ265 ሰዎች ህይወት ደግሞ ማለፉ ተገልጿል።

በትዝታ ደሳለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.