Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል በ25 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በጆር ወረዳ ኡንጎጊ ከተማ በ25 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡

የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጅሉ እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል።

ፕሮጀክቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ኤሌክትሪክ ለሁሉ በሚል ከሚሰሩት 12 ኦፍ ግሪድ ቴክኖሎጂዎች አንዱ ሲሆን፥ ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ርቀው ለሚገኙ አካባቢዎች ኤሌክትሪክን ለማድረስ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተሠራ ሲሆን ከ1 ሺህ በላይ ለሆኑ አባዎራዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ማድረስ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጅሉ ክልሉ ከመሰረተ ልማት ርቆ መቆየቱን አንስተው፥ ከቅርብ አመታት ወዲህ የልማት ተጠቃሚ ሆኖ በክልሉ አንፃራዊ ለውጥ መታየቱን ተናገግረዋል።

በታምሩ ከፈለኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.