Fana: At a Speed of Life!

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ አባ ዱላ ገመዳ እና ለአቶ አብዱላሂ አሊ ሸሪፍ የክብር ዶክትሬት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ አባ ዱላ ገመዳ እና ለአቶ አብዱላሂ አሊ ሸሪፍ የክብር ዶክትሬት አበርክቷል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ በጤናና በህክምና ሳይንስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ከአምስት መቶ በላይ ተማሪዎችን ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርስቲው በአጠቃላይ 573 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፤ 161ዎቹ በህክምና በዶክትሬት ዲግሪ የተመረቁ ናቸው፡፡

አቶ አብዱላሂ አሊ ሸሪፍ ለሃገራቸውና ለህዝባቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት፤ በተለይም በቅርሶች ጥበቃና በሀረር ከተማ የግል ሙዚየምን ያቋቋሙ በመሆኑ የክብር ዶክተሬቱ ተበርክቶላቸዋል፡፡

አቶ አባዱላ ገመዳ በመንግስት የተለያዩ የስራ የኃላፊነት የማህበረሰቡ ህይወት እንዲለወጥ አመራር በመስጠት እንዲሁም በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና መስክ፣ በስነ ሰብና ህብረተሰብ ሳይንስ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ተሰጥቷቸዋል፡፡

በ2012 ዓ.ም መመረቅ የነበረባቸውና በኮቪድ 19 ሳቢያ ሳይመረቁ የቀሩ ተማሪዎችን በሦስተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲና በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በነርስነት፣ በፋርማሲና በህብረተሰብ ጤና ዘርፍ ያስመረቀው፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ያደታ ደሴ፤ ኮሌጁ የተቋቋመበትን 25ኛ ዓመት እያከበረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ ምረቃ በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ፤ ዩኒቨርስቲው የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራምን ወደ 74፣ የድህረ ምረቃን ወደ 99፣ የዶክትሬት ዲግሪን ወደ27 የትምህርት አይነቶች አሳድጎ ሃገራችን የሚያስፈልጋትን የሰለጠ የሠው ኃይል እያፈራ ይገኛል ብለዋል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፤ ጤናው የተጠበቀ ህዝብ እንዲኖር በቀሰማችሁት የጤና ሙያ ህብረተሰቡን ልታገለግሉና ህዝቡ በጤና ችግሮች ተጠቂ እንዳይሆን ሚናችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 30 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት በ13 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ17 የሁለተኛና በ4 የዶክትሬት ዲግሪ እንዲሁም በስድስት የስፔሻሊቲ የትምህርት መርሃ ግብሮች ተማሪዎችን እያሰለጠነ ሲሆን፤ ባለፉት 23 ዓመታት ከ15ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎችን አሰልጥኖ በማስመረቅ ወደ ስራ ማሰማራቱ ተገልጿል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.