Fana: At a Speed of Life!

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የጥራት መጓደል ችግር ፈታኝ እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሁን ላይ የሚታየው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የጥራት መጓደል ችግር ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከብሄራዊ ሥነ ልክ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በክልልና በከተማ አስተዳደሮች ከሚገኙ የኮንስትራክሽን ላቦራቶሪ ማዕከላት ለተውጣጡ አመራርና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በሃገሪቱ የሚከናወነው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ እመርታ የማሳየቱን ያህል በውስጡ እየታየ ባለው የጥራትና የደህንነት ችግር በሰው፣ በአካባቢ፣ በኢኮኖሚ እና በሀገር ላይ ፈተናዎች እየደቀነ መምጣቱን በሚኒስቴሩ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አሰራር ማሻሻያ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ተገኘ ገልፀዋል።

በመሆኑም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሚታየውን የጥራት መጓደል ችግር ለመቅረፍ እና በዘርፉና በሀገር ላይ እየታየ ያለውን ውድመት ለመታደግ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ያሉበትን ማነቆዎች ለመፍታት የኮንስትራክሽን ላቦራቶሪዎችን አቅም መገንባትና የአሰራር ስርዓት ቀርፆ ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በስልጠናው ላይ በኮንስትራክሽን ቤተ መከራዎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ክፍተቶችን በመዳሰስ የአገልግሎቱን ጥራት ለማስጠበቅ በመሳሪያዎቹ አጠቃቀምና አያያዝ እንዲሁም የልኬት አገልግሎት እና የተበላሹ የቤተ ሙከራ መሳሪያዎች ጥገና እንደሚደረግ መገለፁን ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.