Fana: At a Speed of Life!

ዓለምፀሐይ “አድርጉ” አላለችንም፤ ራሷ ያሰበችውን በተግባር ፈፅማ አሳይታናለች – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር “ዓለምፀሐይ “አድርጉ” አላለችንም፤ ራሷ ያሰበችውን በተግባር ፈፅማ አሳይታናለች” ብለዋል፡፡

አቶ ደመቀ ይህንን ያሉት ዛሬ የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል የትውውቅና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ማዕከሉ በአንጋፋዋ ከያኒ ዓለምጸሃይ ወዳጆ የተመሰረተ ሲሆን ላለፉት 20 ዓመታት በሰሜን አሜሪካ በኪነ-ጥበብና በትምህርት ላይ ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል።

አቶ ደመቀ በንግግራቸው ማዕከሉ በዋናነት በድፍን ኢትዮጵያ የሚገኙ የባህል፣ የታሪክና የኪነጥበብ ፀጋዎችን ትውልዱ መንዝሮ እንዲጠቀምባቸው በእጅጉ ያግዛል ብለዋል።

በዚህ ዘመን እንደዓለምፀሃይ ታግለው የሚያሸንፉ፤ አሸንፈው ለውጥ የሚያመጡ ጀግኖች በብዛት እንደሚያስፈልጉን ታሪካዊ አጋጣሚው እንደሚያስገነዝብ ገልጸዋል።

ለማዕከሉ ቀጣይነት እና ትርጉም አዘል አገልግሎት ሁላችንም ልንደግፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ዓለምፀሃይ የዕድሜ ዘመን ደማቅ ኪነጥበባዊ አበርክቶዎቿ ብቻ ሳይሆኑ፤  ለትውልዱ መልካም ሰብዕና ግንባታ በእሷ ስም ወደፊት ለሚጠብቁን ትሩፋቶች አስቀድሜ ያለኝን ታላቅ አድናቆት እና ተስፋ ለመግለፅ እወዳለሁ ሲሉ አቶ ደመቀ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.