Fana: At a Speed of Life!

የግብርና መረጃዎችን ማግኘት የሚያስችል ዮያ እርሻ “640” የተሰኘ የጥሪ ማዕከል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና መረጃዎችን ማግኘት የሚያስችል ዮያ እርሻ “640” የተሰኘ የጥሪ ማዕከል ይፋ ሆነ፡፡

የግብርና ጥሪ ማዕከሉ የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው፡፡

የጥሪ ማዕከሉ የአርሶ አደሩን  ምርትና ማርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተሰማ ገብረ መድህን ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረትም  ማዕከሉ ለአርሶ አደሩ የገበያ መረጃዎችን፣ የአየር ንብረት ሁኔታ  እና  ግብርና ነክ የባለሙያ  ምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡

በተጨማሪም  አርሶ አደሮችን ከግብርና ግብዓት አቅራቢዎች ፣ ከምርት ተረካቢዎች እና  ከግብርና ማሽነሪ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር  በማገናኘት አርሶ አደሮችን ካላስፈላጊ እንግልት እና ወጪ ያድናል ተበሏል፡፡

የጥሪ ማዕከሉን  የግብርና ሚኒስቴር  ከአዋሽ አግሪ ቴክ  ጋር በመተባበር  ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጽዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.