Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ፣ አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከቀጠናው የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል የሚገኘውን ኮላይጅ የስደተኞች ካምፕ ጎብኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚንስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ከቀጠናው የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል የሚገኘውን ኮላይጅ የስደተኞች ካምፕ ጎብኙ፡፡

ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ትልቁን ቁጥር የሚሸፍኑ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች የሚገኙበት ካምፕ በመሆኑ አቅም በፈቀደ  ወደ ቀደመው አኗኗር እንዲመለሱ እና ሰላማቸውና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን የዓለም ባንክ ዳይሬክተር የሆኑት ኡስማን ዲዮን በበኩላቸው የተፈናቃዮቹ ተወካዮቹ ያነሷቸውን ጉዳዮች በሚገባ ማድመጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ኡስማን ዲዮን የተጠቀሱት ችግሮች ሁሉ መቅረፍ ባይቻልም ከሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በመምከር ትርጉም ያለው ስራ ለመስራት ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡

በዕለቱ በካምፑ ለተፈናቀሉ ዜጎች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች መመልከታቸውን ከሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.