Fana: At a Speed of Life!

10ኛው አባይ ናይል ማራቶን ህዝባዊ የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው አባይ ናይል ማራቶን ህዝባዊ የሩጫ ውድድር በባህርዳር ከተማ ተካሄደ፡፡
በውድድሩ አንጋፋና ተተኪ አትሌቶች ከአዲስአበባ ፣ከአማራ ክልል እንዲሁም ከሌሎች ክልሎች መሳተፋቸውን የውድድሩ አዘጋጅ አትሌት መልካሙ ተገኘ ተናግረዋል፡፡
ውድድሩ ተተኪ አትሌቶች ለማፍራት ፣የአባይ ናይል ሩጫን ለአለም ለማስተዋወቅ እንዲሁም የባህርዳር ከተማ የስፓርት ቱሪዝምን ለማሳድግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውድድሩ በወንዶች ግዜአለሁ አበጀ ከአዲስአበባ መብራት ሀይል አትሌቲክስ ክለብ በቀዳሚነት ውድድሩን ሲያጠናቅቅ ፣ ወርቅነህ አዳና ከምዕራብ ጎጃምአትሌቲክስ ክለብ እንዲሁም መንግስቱ አማራ ከእንጅባራ አትሌቲክስ ፕሮጀከት በግል ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
በሴቶች አዲስአለም እያዩ ከደባርቅ ዋሊያ አትሌቲክስ ክለብ፣አድሴ ምስለኔ ከአማራ ፓሊስ አትሌቲክስ ክለብ ፣ ትግስት ጌትነት ከአዊ ልማት ማህበር አትሌቲክስ ክለብ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
ለአሸፊዎችም የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል፡፡
በናትናኤል ጥጋቡ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.