Fana: At a Speed of Life!

የዋና ስፖርት ዳኛ ኢንስፔክተር ሲሳይ ወየሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው የውሃ ዋና ስፖርት ዳኛ ኢንስፔክተር ሲሳይ ወየሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

በኢትዮጵያ ውሃ ዋና ስፖርት ውስጥ በዳኝነትና በአሰልጣኝነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት ኢንስፔክተር ሲሳይ ወየሳ ዛሬ በድንገት ሕይወታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል።

ኢንስፔክተር ሲሳይ የኦሮሚያ ፖሊስ ባልደረባ የነበሩ ሲሆኑ የኦሮሚያ ፖሊስ የውሃ ዋና ክለብ እንዲቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሰው ናቸው ተብሏል፡፡

የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን በአንጋፋው ዳኛ ኢንስፔክተር ሲሳይ ወየሳ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

 

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.