የሀገር ውስጥ ዜና

ሸሙ የምግብ ዘይት ፋብሪካ የማስፋፊያ ስራውን አጠናቆ በቀን 950 ቶን ዘይት ማምረት ጀመረ

By Tibebu Kebede

March 14, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር የማስፋፊያ ስራ ሲከናወንለት የቆየው የሸሙ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት የምግብ ዘይት ፋብሪካ በቀን 950 ቶን ዘይት ማምረት ጀመረ።

ድርጅቱ በድሬዳዋ ከተማ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የምግብ ዘይት ምርት የጀመረ ቢሆንም፤ የዘርፉን ፍላጎት በሚመጥን ደረጃ ለማምረት እንዲችል የማስፋፊያ ስራ ሲያከናውን መቆቱ ተጠቁሟል።

የሸሙ ማኔጅመንት ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሬዘር ደበላ እንዳሉት፤ድርጅቱ በ2010 የመጀመሪያና ቀዳሚ በመሆን130 ቶን ዘይት በቀን ማምረት መጀመሩን አስታውሰዋል።

ሆኖም ፍላጎቱ በመጨመሩ የማስፋፊያ ስራው ሲከናወን ቆይቷል ብለዋል።

ድርጅቱ በቀን 1 ነጥብ 18 ሚሊየን ቶን ግብዓት በቀን ውስጥ በመጠቀም 950 ቶን ዘይት ማምረት መጀመሩን ተናግረዋል

በዚህም አንድ ሶስተኛ የሀገሪቱን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችለው ሲሆን አሁንም 3 ሚሊየን ሊትር ዘይት ተመርቶ የንግድ ሚኒስቴር ያስቀመጠውን የዋጋ ተመን በመከተል እንዲከፋፈል በሚኒስቴሩ የተፈቀደላቸው አከፋፋዮች እየተጠበቁ መሆኑን አቶ ተስፋ ሚካኤል ጎሹ አንስተዋል።

በዚህ ወቅት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ብቻ ዘይቱ እየወሰደ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ዘርፉን ለመደገፍ እየተደረገ ባለው የመንግስት ርብርብም እስካሁንም ለጥሬ እቃዎች ማስገቢያ ዶላር መፍቀዱን አስታውቀዋል።

የማስፋፊያ ስራ ለመስራት የቦታ ችግር ፈተና እንደሆበነበት እና ይህ አንዲፈታም ጠይቋል።

ሸሙ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከ28 ዓመታት በፊት በተለያዩ ምርቶች ገበያውን የተቀላቀለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 15 ኩባንያዎችን በስሩ በማቀፍ ዘይትን እና ሳሙናን ጨምሮ የተለያዩ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል።

እስካሁንም ለ850 የስራ ፍላጊዎች ስራ የፈጠረ ሲሆን በቀጣይነት እስከ 1 ሺህ 500 ለማድረስ እየሰራሁ ነው ብሏል።

እስካሁንም ድርጅቱ ያመረተው 3 ሚሊየን ሊትር ዘይት አከፋፋዮችን እየጠበቀ ያለ ሲሆን በቀጣይነት ስራውን በተሻለ ለማስፋትም የቦታ ችግር መነቆ ሆኖብኛል ይላል ።

በአፈወርቅ አለሙ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

 

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!