Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ንፋስ ቀለቀቅሎ የጣለ ዝናብ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ፑኩሙ ቀበሌ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል፡፡

ከትናንት በስቲያ ምሽት 5 አካባቢ ንፋስ ቀላቀሎ የጣለው ዝናብ በሶስት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ሲያደርስ፥ 55 የቆርቆሮና 20 የሳር ክዳን በድምሩ 75 መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ አራት የመንግስት ተቋማት ፈራርሰዋል፡፡

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጋትቤል ሙን ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም ኤጀንሲው ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ ይሰራል ማለታቸውን ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ የተመራ ቡድን በስፍራው በመገኘት የደረሰውን ጉዳት ተመልክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.