Fana: At a Speed of Life!

እስከ ቀጣዩ ዓመት ታህሳስ ድረስ 20 በመቶ ዜጎችን የኮቪድ 19 ክትባት ለመከተብ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ ታህሳስ 30 2014 ዓ.ም  ባለው ጊዜ ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች የኮቪድ 19 ክትባት  ለመከተብ እየሰራ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ይህንን ያስታወቁት የጤና ሚኒትር ዴኤታ ዶክተር ደረጃ ዱጉማ ናቸው፡፡

ሚኒስቴሩ ክትባቱን ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መጨመሩንና በቫይረሱ ምክንያት በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት ከፍ እያለ መሆኑን ዶክተር ደረጀ ዱጉማ አስታውሰው አሁንም ህብረተሰቡ ቀደም ሲል ሲደረጉ የነበሩ የጥንቃቄ እርምጃዎቸን በእጅጉ ተግበራዊ ሊያደር ይገባል ብለዋል፡፡

መንግስት በመጀመሪያ ዙር ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ክትባት መረከቡ ይታወሳል፡፡

ባሳለፍነው ቅዳሜም በይፋ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ክትባቱን መስጠት ተጀምሯል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.