ዓለምአቀፋዊ ዜና

በቀድሞው የፓኪስታን ፕሬዚዳንት ፐርቬዝ ሙሻራፍ ላይ የተላለፈው የሞት ቅጣት ተነሳ

By Tibebu Kebede

January 13, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀድሞው የፓኪስታን ፕሬዚዳንት ፐርቬዝ ሙሻራፍ ላይ ተላልፎ የነበረው የሞት ቅጣት በሀገሪቱ ፍርድ ቤት እንዲነሳ ተወሰነ።

ፍርድ ቤቱ በሙሻራፍ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ህገ መንግስታዊ ሂደቱን የተከተለ አይደለም በሚል ነው ውድቅ ያደረገው።

የላሆሬ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፓኪስታንን ከፈረንጆቹ 2001 እስከ 2008 የመሯትን ሙሻራፍ በመደገፍ ውሳኔ አሳልፏል።

አንድ ጠበቃም ውሳኔው ሙሻራፍ ነፃ ሰው እንደነበሩ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሙሻራፍ ባለፈው ታህሳስ ወር የተላለፈባቸውን የሞት ቅጣት ውሳኔ ህገ ወጥ ነው ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ለውሳኔው መሻር የቀረቡ ጠበቃዎች ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ማስረጃ፣ የፍርድ ቤቱ ህጋዊነት እና የተመረጡት ጠበቆች ህገ ወጥ ናቸው መባል ምክንያት መሆኑን ኢሽጣቅ ካህን የተባሉ የመንግስት ጠበቃ ተናግረዋል።

እንደ ጠበቃው ገለፃ ከአሁን በኋላ እርሳቸውን የሚቃወም ዳኝነት አይኖርም ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ