Fana: At a Speed of Life!

በጄኔቫ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት ያለውን ትክክለኛ ሁኔታ ለማሳወቅና ጣልቃ ገብነትን በመቃወም የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።

ሰልፈኞቹ የአንድ አገር ሉዓላዊነት ሊከበር እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተለይም የህውኃት ደጋፊዎች በሚያሰራጩት ሃሰተኛ መረጃ የተነሳ በኢትዮጵያ ላይ ተገቢ ያልሆኑ ጫናዎች እየተፈጸሙ ነው ያሉት የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ትክክለኛ መረጃ በመያዝ የሚያካሂዱትን ጫና ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል።

ሰልፈኞቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ በህውኃት ደጋፊዎች ሃሰተኛ መረጃ የተሳሳተ ግንዘቤ መውሰድ እንደሌለባቸውም መማልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.