Fana: At a Speed of Life!

በየካቲት ወር ከ21 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በየካቲት ወር ከ21 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ዘንድሮ የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ12 በመቶ በላይ ዕድገት ማሳየቱ ተጠቅሷል፡፡

ሚኒስቴሩ የገቢ አሰባሰቡ ስኬታማ እንደነበረ ቢገልጽም የማይከፍሉ ዜጎችም እንዳሉም አንስቷል፡፡

ደረሰኝ አለመቁረጥ፣ የግብይት ዋጋ አሳንሶ ደረሰኝ መቁረጥ፣ በሀሰተኛ ማንነት የፈጠራ ድርጅቶችን በመመስረት ሀሰተኛ ደረሰኝ አሳትሞ መጠቀምና መሸጥ፣ ወጭን ማሳበጥ እንዲሁም ሆነ ብሎ ገቢን መቀነስና ግብርን ለማሸሽና ለመሰወር የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸውም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሚኒስቴሩ ግብራቸውን በወቅቱ በማስታወቅ ለከፈሉ ግብር ከፋዮች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.