Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የሞምባሳ ወደብን ልትወርስ ትችላለች መባሉን መንግስት አስተባበለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ ለባቡር መንገድ ግንባታ ከቻይና የተበደረችውን ከፍተኛ ገንዝብ መመለስ ካልቻለች ቤጂንግ የሞምባሳ ወደብን ልትወርስ ትችላች መባሉን የሀገሪቱ መንግስት አስተባበለ።

472 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የባቡር መንገድ ወጪ መጀመሪያ ከታቀደለት በአራት እጥፍ እና ከዓለም አቀፍ ደረጃው የሶስት እጥፍ ብልጫ እንዳለው ተነግሯል።

በኬንያ የሚገኝ ጋዜጣ በትናንትናው ዕለት፥ ኬንያ ከቻይና የተበደረችውን 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር መመለስ ካልቻለች ቻይና የሞምባሳን ወደብ ልትወርስ ትችላለች የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር።

የኬንያ ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱ በቻይናም ይሁን በሌላ ሀገር የሞምባሳን ወደብ የምታጣበት ምክንያት የለም ብሏል።

ለፕሮጀክቱ ከቤጂንግ የተገኘው ብድርም የሃገሪቱ ፓርላማ ሳያፀድቀው በተለየ መንገድ  ሊከፈል አይችልም ሲልም ነው ሚኒስቴሩ በመግለጫው ያመለከተው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.