Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ቲቦር ናዥ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ቲቦር ናዥ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአምስት የአፍሪካ ሃገራት ጉብኝት ያደርጋሉ።

ረዳት ፀሃፊው ከረቡዕ ጀምሮ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ነው ጉብኝታቸውን የሚያደርጉት።

በጉብኝታቸው መልካም አስተዳደር እና ጠንካራ የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር፣ ሙስናን ለመዋጋት፣ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን እንዲሁም ንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፋትና ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

በቆይታቸው ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች፣ ከሲቪክ ማህበራት ተወካዮች እና ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎም ነው የሚጠበቀው።

የረዳት ፀሃፊው ጉብኝት አሜሪካ ከምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን ፍላጎት ያሳያል መባሉን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጫ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.