የሀገር ውስጥ ዜና

ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ ለ80ኛ ጊዜ ደም በመለገስ ቀዳሚ ሆኑ

By Abrham Fekede

March 16, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ ለ80ኛ ጊዜ ደም በመለገስ ቀዳሚ ሆኑ፡፡

የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ገጻቸው ይህ በኢትዮጵያ ሴት ደም ለጋሾች ዘንድ ክብረ ወሰን ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ እናትም ቀዳሚ ደም ለጋሽም በመሆን በዛሬ ዕለት የሴቶች ቀንን በማስመልከት ደም መለገሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሯ ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ ለ80ኛ ጊዜ ደም መለገሳቸውን አስመልከተው “እንኳን ደስ አለሽ! እናመሰግናለን!” ብለዋቸዋል፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!