የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በተቋማት ጥራት ያለው ምርት እና አገልግሎትን ማቅረብ እንደሚገባ ተናገሩ

By Tibebu Kebede

March 18, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በግልም ሆነ በመንግስት ተቋማት ጥራት ያለው ምርት እና አገልግሎትን ማቅረብ እንደሚገባ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ከኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የቦርድ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ድርጅቱ እያከናወናቸው ባሉ ተግባራትና ማሻሻያዎች ዙሪያ መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዚህ ወቅትም በተቋማት ጥራት ያለው ምርት እና አገልግሎት ማቅረብ ይገባል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!