Fana: At a Speed of Life!

ወላይታ ድቻ የቀድሞ አሰልጣኙ ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ጥር 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ የቀድሞ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ።

ክለቡ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ በ8ኛ ሳምንት በሜዳቸው ላይ መሸነፋቸውን ተከትሎ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙበትን ማስረጃ በመያዝ ወደ ምድብ ስራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡን አስታውቋል።

ክለቡ በቀጣይ ከጅማ አባጅፋር ጋር ለሚኖረው ጨዋታ አሰልጣኙ ቡድኑን በማዘጋጀት ወደ ጅማ ይዘው እንዲጓዙም ነው ጥሪ ያቀረበው።

የክለቡ የስራ አመራር ቦርድ በቡድኑ ውጤት ማጣት እና በደጋፊዎች ከፍተኛ ተቋውሞ ምክንያት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ አሰልጣኙ ለረዥም ጊዜ በስራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው ስራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ተቆጥሮ በምክትላቸው አሰልጣን ደለለኝ መተካቱ ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈም የቡድን አመራሮችን እና 3 ተጫዋቾችን ማስጠንቀቁ ይታወሳል፤ በወቅቱ የተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ አሰልጣኙ ስራዬን አለቀኩም፤አሁንም የቡድኑ ህጋዊ አሰልጣኝ ነኝ ማለታቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.