ቢዝነስ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከኤች ኤንድ ኤም ተወካዮች ጋር በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ዙሪያ ተወያየ

By Tibebu Kebede

March 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ከኤች ኤንድ ኤም ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ለዘርፉ እድገት እና የተቀመጡ ሁሉን አቀፍ የልማት ግቦችን ለማሳካት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ኤች ኤንድ ኤም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ልማት ለኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋር ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!