ቢዝነስ

ስምንተኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ማህበራት አውደ ርዕይና ባዛር ተከፈተ

By Tibebu Kebede

March 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስምንተኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት አውደ ርዕይና ባዛር ዛሬ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ተከፍቷል።

አውደ ርዕዩና ባዛሩ እስከ መጋቢት 14 ቀን ድረስ የሚቆይ ሲሆን ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ 66 የህብረት ስራ ማህበራትና 15 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ይዘው በመቅረብ እየተሳተፉበት ነው።

በባዛሩ ላይ ከ500 በላይ የግብርና ምርት ዓይነቶች ቀርበዋል ተብሏል።

ከ4 እስከ 5 ሺህ ኩንታል የግብርና ምርቶችም በቀጥታ ለሽያጭ መቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን ከ20 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ደግሞ የግብይት ስምምነት እንደሚፈፀም ይጠበቃል።

ይህ አውደ ርዕይ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የዋጋ ንረትን በማረጋጋት በኩል ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ተገልጿል።

አውደ ርዕዩንና ባዛሩን 50 ሺህ ያህል ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢብኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!