ስፓርት

ባርሴሎና አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን በማሰናበት ኪኬ ሴቲዬን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል

By Tibebu Kebede

January 14, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስፔኑ ሀያል የእግር ኳስ ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን በማሰናበት ኪኬ ሴቲዬን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ተሰምቷል።

የ55 ዓመቱ አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ባርሴሎናን በመሩበት ጊዜ ክለቡ ሁለት የስፔን ላሊጋ ዋንጫዎችን እንዲያነሳ እና የዘንድሮውን የላሊጋ ውድድር በግብ ልዩነት እንዲመራ አድርገዋል።

ሆኖም ግን የካታላኑ የክለብ አመራሮች ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ባርሴሎናን ለአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ማድረስ አልቻሉም በሚል ከክለቡ እንዲሰናበቱ ማድረጋቸው ነው የተነገረው።

ባርሴሎና አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ምትክም የ61 ዓመቱን የቀድሞ የሪያል ቤቲስ አሰልጣኝ ኪኬ ሴቲዬን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ነው የተነገረው።

አሰልጣኝ ኪኬ ሴቲዬን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2005 ጀምሮ ሪያል ቤቲስን በአሰልጣኝነት በመሩበት ዘመንም ትልቁ ስኬታቸው ክለቡን ለኮፓ ዴልሬይ የግማሽ ፍፃሜ ማድረሳቸው ብቻ እንደሆነም ተነግሯል።

አሁን ላይ ባርሴሎናል ለማሰልጣን የተሾሙት አሰልጣኝ ኪኬ ሴቲዬን ክለቡን ለሁለት ዓመት ተኩል ለመምራት መስማማታቸውም ታውቋል።

ምንጭ፦ www.bbc.com