የሀገር ውስጥ ዜና

የምርምር ስራዎች የምርምር ስነምግባር መርሆዎችን ተከትለው እንዲሠሩ የሚያስችል ስልጠናዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

March 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርምር ስራዎች የምርምር ስነምግባር መርሆዎችን ተከትለው እንዲሠሩ በተቋማት የሚገኙ የምርምር ስነምግባር ኮሚቴዎችን አቅም መገንባትና ማጠናከር የሚያስችል ስልጠናዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ስልጠናው ከፍተኛ የትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በመሠረታዊ፣ በሳይንስና በጥናትና ምርምር የጎለበቱ እንዲሆኑ የሚያስችል ስልት ለመንደፍ ያስችላል ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም የምርምሮቹ ውጤቶች በስራ ላይ የሚውሉበትን መንገድ ለማመቻቸት ይረዳልም ነው የተባለው፡፡

ስልጠናው ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያዘጋጁት ነው፡፡

በሰላማዊት ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!