የሀገር ውስጥ ዜና

የድሬዳዋ ብልፅግና ፖርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መረሃ ግብር አካሄደ

By Abrham Fekede

March 31, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የድሬዳዋ ብልፅግና ፖርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መረሃ ግብር አካሄደ፡፡

በማስጀመሪያ መረሃ ግብሩ ላይ ድሬዳዋ ያላትን መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ በመጠቀም የኢንዱስትሪ፣ የደረቅ ወደብና የንግድ ማዕከል ለማድረግ ፖርቲው እንደሚሰራ አስታውቋል።

የብልጽግና ፖርቲ ከሁሉም በሁሉም ለሁሉም ያሉት የድሬዳዋ ብልፅግና ፖርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ ፖርቲው በቀጣዩ ምርጫ ለመወዳደር ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ምረጡኝ ቅስቀሳ መግባታቸውን አስታዉቀዋል።

በከተማዋ አራት አቅጣጫዎች የተጀመረው የምረጡኝ ቅስቀሳው ከሰዓት በውይይት እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!